jenber - yirdaw tenawe lyrics
አልገለጥ አለ ተጋርዶ ሰፈሯ
ቀረች ከህዋው ላይ ከጠረፍ ድንበሯ
ምን ይሆን የፀሀይ ማፈሯ
ምን ይሆን የጀምበር ማፈሯ
ምን ይሆን የፀሀይ ማፈሯ
ምን ይሆን የጀምበር ማፈሯ
አልገለጥ አለ ተጋርዶ ሰፈሯ
ቀረች ከህዋው ላይ ከጠረፍ ድንበሯ
ምን ይሆን የፀሀይ ማፈሯ
ምን ይሆን የጀምበር ማፈሯ
ምን ይሆን የፀሀይ ማፈሯ
ምን ይሆን የጀምበር ማፈሯ
ነይ ፀሀይ የአድማስ መጋረጃሽ ፀሀይ
በሽንፈት ሲከለል
ነይ ፀሀይ አንቺን ለመሰወር ፀሀይ
ዳመናው ሲቆለል
ነይ ፀሀይ ጠፈሩን ባልዳኘው ፀሀይ
ህዋው ባይከሰስ
ነይ ፀሀይ እጠብቅሻለሁ ፀሀይ
ያንቺ ቀን እስኪደርስ
የንጋት የጠዋት ሙቀቴን
አስጥላኝ የምሽት መብራቴን
እንደምን ልቁረሰው እራቴን
አላውቀው ጓዳዬን ማጀቴን
የንጋት የጠዋት ሙቀቴን
አስጥላኝ የምሽት መብራቴን
እንደምን ልቁረሰው እራቴን
አላውቀው ጓዳዬን ማጀቴን
አልገለጥ አለ ተጋርዶ ሰፈሯ
ቀረች ከህዋው ላይ ከጠረፍ ድንበሯ
ምን ይሆን የፀሀይ ማፈሯ
ምን ይሆን የጀምበር ማፈሯ
ምን ይሆን የፀሀይ ማፈሯ
ምን ይሆን የጀምበር ማፈሯ
ነይ ፀሀይ ከሰው ተደብቀሽ ወዴት
ለማን ልትበጂ
ነይ ፀሀይ ያንቺማ መገለጥ ፀሀይ
ለኔ ነበር እንጂ
ነይ ፀሀይ ጠፈሩን ባልዳኘው ፀሀይ
ህዋው ባይከሰስ
ነይ ፀሀይ እጠብቅሻለሁ ፀሀይ
ያንቺ ቀን እስኪደርስ
እምቁን ግለጪው አውጥተሽ
ጨለማን በብርሃን ተክተሽ
አጫውጪኝ በይ እንዳስለመድሺኝ
በኩርፊያ ጭጋግ አታውርሺኝ
አልገለጥ አለ ተጋርዶ ሰፈሯ
ቀረች ከህዋው ላይ ከጠረፍ ድንበሯ
ምን ይሆን የፀሀይ ማፈሯ
ምን ይሆን የጀምበር ማፈሯ
ነይ ፀሀይ የአድማስ መጋረጃሽ ፀሀይ
በሽንፈት ሲከለል
ነይ ፀሀይ አንቺን ለመሰወር ፀሀይ
ዳመናው ሲቆለል
ነይ ፀሀይ ጠፈሩን ባልዳኘው ፀሀይ
ህዋው ባይከሰስ
ነይ ፀሀይ እጠብቅሻለሁ ፀሀይ
ያንቺ ቀን እስኪደርስ
የንጋት የጠዋት ሙቀቴን
አስጥላኝ የምሽት መብራቴን
እንደምን ልቁረሰው እራቴን
አላውቀው ጓዳዬን ማጀቴን
እምቁን ግለጪው አውጥተሽ
ጨለማን በብርሃን ተክተሽ
አጫውጪኝ በይ እንዳስለመድሺኝ
በኩርፊያ ጭጋግ አታውርሺኝ
የንጋት የጠዋት ሙቀቴን
አስጥላኝ የምሽት መብራቴን
እንደምን ልቁረሰው እራቴን
አላውቀው ጓዳዬን ማጀቴን
እምቁን ግለጪው አውጥተሽ
ጨለማን በብርሃን ተክተሽ
አጫውጪኝ በይ እንዳስለመድሺኝ
በኩርፊያ ጭጋግ አታውርሺኝ
Random Song Lyrics :
- what i have done - admiral james t lyrics
- face in my hands - el radio fantastique lyrics
- flexim beyamit 2000 - פלקסים בימית 2000 - nanach classy - ננח קלאסי lyrics
- censura - raffa augusto lyrics
- goon$ - duwap kaine lyrics
- blue - atheabstract lyrics
- мой чейн (my chain) - yung svturn lyrics
- indigo - gustalba lyrics
- the hummingbird - josh pyke lyrics
- jeva - gaby luna lyrics