አፄ ቴዎድሮስ (atse tewodros) - tedy afro lyrics
የሰገደላት ዉበቱን
ያቺን የቃል መስታየት
ሞቶ ቀደማት ቴዎድሮስ
ቆሞ ስቃይዋን ላለማየት
የሰገደላት ዉበቱን
ያቺን የቃል መስታየት
ሞቶ ቀደማት ቴዎድሮስ
ቆሞ ስቃይዋን ላለማየት
ኸ… ሲል ናና …
ደርሶ ባያስጥለው ገብርዬን ከስለት
ጀግናው ተፈተነ በመቅደላ አቀበት
ተዋከበና ተዋከበና
ወዲህ ዞር ቢል ሰው የለምና
ገብርዬ ሲወድቅ ቀኙ ዛለና
አረሩን ስቦ ጠጣው ያ ጀግና
አላይ አለና
ሞተ ወይ ያጀግና
አላይ አለና
ሞተ ወይ ያጀግና
ኸ… ሲል ናና …
ደርሶ ባያስጥለው ገብርዬን ከስለት
ጀግናው ተፈተነ በመቅደላ አቀበት
ተዋከበና ተዋከበና
ወዲህ ዞር ቢል ሰው የለምና
የነደደ እሳት ክንዱን ተርሶ
ጨክኖ ካሳ ጋተና ኮሶ
ሞተ ላንድ አገር ባንዲራ ለብሶ
አላይ አለና
ሞተ ወይ ያጀግና
አላይ አለና
ሞተ ወይ ያጀግና
አላይ አለና
ሞተ ወይ ያጀግና
አላይ አለና
ሞተ ወይ ያጀግና
ካሳ በል አግሳ እንደ አንበሳ
የቕራ አንበሳው ዳግማሮስ ካሳ በል አግሳ
ካሳ በል አግሳ እንደ አንበሳ
ያንዲት እናት ሀገር ክብርዋ ከቶም ሳይረሳ
ካሳ በል አግሳ እንደ አንበሳ
ንቃ በመንፈስ ላንድነት ካሳ ተነሳ
ካሳ በል አግሳ እንደ አንበሳ
አንተ የሞትክላት ሀገር ክብርዋ ሳይረሳ
ካሳ በል አግሳ እንደ አንበሳ
አላይ አለና
ሞተ ወይ ያጀግና
አላይ አለና
ሞተ ወይ ያጀግና
ኦ…
ጎንደር ጎንደር የቴዎድሮስ አገር
ያንዲት ኢትዮጵያ ዋልታና ማገር
ነፍሱን የሰጣት ለካ አለም ንቆ
አገር ሊያቆም…
Random Song Lyrics :
- manipulator - scriptor & djbz lyrics
- nemirna - tropico band lyrics
- calm eyes fixed on me, screaming - draw the emotional lyrics
- я как котик в твоем сне - lowlayt, seshbaby lyrics
- embaixo das estrelas - theus lyrics
- the glass is filled with disinfectant - mushroom dwellers lyrics
- alone - ava max lyrics
- voces - mauser lyrics
- what’s wrong with me? - anthony callea lyrics
- dsl - shooda lyrics