lirikcinta.com
a b c d e f g h i j k l m n o p q r s t u v w x y z 0 1 2 3 4 5 6 7 8 9 #

egnan new mayet - tamrat desta lyrics

Loading...

ናፍቆት ሃሳብ ሰቀቀኑ ምኞት የሚቀረው
በአይነ ስጋ ፍቅሬ መቼ ነው አይንሽን የማየው
ናፍቀሽኛል እኔ ብትርቅኝ ኑሮ ቢለየን

ይቅናሽ እንጂ አንቺን ደግሞ አይቀርም እንገናኛለን

እኛ ነው ማየት ስትመጪ እሱ ብሎት
ለጉድ ተናንቀን በእንባ አንገት ላንገት
ሰው አያግደን ዘመድ አዝማድ ቢኖር
ናፍቆት ነውና የተራብነው ፍቅር

እኛ ነው ማየት ስትመጪ እሱ ብሎት
ለጉድ ተናንቀን በእንባ አንገት ላንገት
ሰው አያግደን ዘመድ አዝማድ ቢኖር
ናፍቆት ነውና የተራብነው ፍቅር

አቤት መቼም ይታየኛል
ሳትመጪ ካሁኑ ታውቆኛል
አንቺን በአካል አግንቼ
በናፍቆት ማንባቴን ረስቼ
ጎኔ ሲጠገን ጉልበቴ
መለስ ሲልልኝ ጉዳቴ
ላገር ሲታይ ትዕግስታችን
በፅናት የቆየው ፍቅራችን

በሃሳብ ይታየኝና እረካለው እረካለው
ያችን ቀን እስከማያት ናፍቃለው ናፍቄያለሁ
በሃሳብ ይታየኝና እረካለው እረካለው
ያችን ቀን እስከማያት ናፍቃለው ናፍቄያለሁ

እኛ ነው ማየት ስትመጪ እሱ ብሎት
ለጉድ ተናንቀን በእንባ አንገት ላንገት
ሰው አያግደን ዘመድ አዝማድ ቢኖር
ናፍቆት ነውና የተራብነው ፍቅር

ያብቃሽ ነይ እንጂ ቀንቶሽ
ለናፈቅሻት ለሃገር ምድርሽ
ያን ቀን እኛ ነው ማየት
ገና እግረሽ ሲረግጥ መሬት
ጋርዶን እምቁ ናፍቆት
የምን ስጋት የምን ፍርሃት
በእንባ አንገት ለአንገት
ተናንቀን በፍቅር ስንዘምት

በሃሳብ ይታየኝና እረካለው እረካለው
ያችን ቀን እስከማያት ናፍቃለው ናፍቄያለሁ
በሃሳብ ይታየኝና እረካለው እረካለው
ያችን ቀን እስከማያት ናፍቃለው ናፍቄያለሁ

Random Song Lyrics :

Popular

Loading...