lirikcinta.com
a b c d e f g h i j k l m n o p q r s t u v w x y z 0 1 2 3 4 5 6 7 8 9 #

maranata - mesfin gutu lyrics

Loading...

አስሩ ፡ ቆነጃጅቶች ፡ ሙሽራውን ፡ ሲጠብቁ
አምስቱ ፡ ልባሞች ፡ ነበሩ
አምስቱ ፡ ደግሞ ፡ ሰነፎች

ታዲያ ፡ አንተ ፡ ከየትኛው ፡ ነህ
አንቺስ ፡ እህቴ ፡ ሆይ
ሙሽራው ፡ በደጅ ፡ ነው
ለኩስ ፡ ኩራዝህን ፡ ለኩሽ ፡ ኩራዝሽን

አዝ፦ ማራናታ ፡ አሜን ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ሆይ ፡ ቶሎ ፡ ና (፫x)
ናፍቆታችን ፡ አሜን ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ሆይ ፡ ቶሎ ፡ ና
ማራናታ (ቶሎ ፡ ና) ፡ አሜን ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ሆይ ፡ ቶሎ ፡ ና

የዚህ ፡ ዓለም ፡ መከራ ፡ እጅግ ፡ ቢበረታ
ሙሽራው ፡ በደጅ ፡ ነው ፡ ሊመጣ
እስኪ ፡ እንበል ፡ ማራናታ

አዝ፦ ማራናታ ፡ አሜን ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ሆይ ፡ ቶሎ ፡ ና
ማራናታ ፡ አሜን ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ሆይ ፡ ቶሎ ፡ ና
ሙሽራ ፡ ሆይ ፡ ቶሎ ፡ ና ፡ ቶሎ ፡ ና
ሙሽራ ፡ ሆይ ፡ ቶሎ ፡ ና (፬x)

እረፍት ፡ የተጠራ ፡ እንደኛ ፡ ማነው
በምድር ፡ ተቀምጦ ፡ በሠማይ ፡ ርስት ፡ ያለው ፡ (ርስት ፡ ያለው (፪x))
እንሄዳለን ፡ አዲሲቱ ፡ ሃገር ፡ (ሃገር ፡ ሃገር ፡ ሃገር ፡ አለኝ)
አገር ፡ አለኝ ፡ በሠማይ (በሠማይ)
ከበጉ ፡ ጋር ፡ በደስታ ፡ ልንኖር (ልንኖር)
ሙሽራው ፡ ሊመጣ ፡ በደጅ ፡ ነው (በደጅ ፡ ነው (፪x))
በደጅ ፡ ነው ፡ በደጅ ፡ ነው (በደጅ ፡ ነው)

አዝ፦ ማራናታ (ቶሎ ፡ ና ፡ ቶሎ ፡ ና)
አሜን ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ሆይ ፡ ቶሎ ፡ ና (፬x)

Random Song Lyrics :

Popular

Loading...