kulun - lij michael lyrics
አይኗን ቀጠን አርጋ ተኩላው (ተኩላው)
አይኗን ዐየ ጎበዝ አይኑን ቢያመው መንገድ ሳተ (ሳተናው)
አይኗን ቀጠን አርጋ ተኩላው (ተኩላው)
አይኗን ዐየ ጎበዝ አይኑን ቢያመው መንገድ ሳተ (ሳተናው)
አይነ ጉብል አንቺ ሎጋ
በእኔ ዜማ እስኪ እናውጋ
አይንሽን ተኩለሽ ወተሽ
ፍቅርን መውደድን ይዘሽ
ነግሬሽ ነበር ብዬሽ
በስንቱ ተከቧል በርሽ
መፈንቅለ ፍቅር ሞክረው
ከሸፈልሽ አሉ ኩ ዴታው
አይተኛም አይደል ወይ ስሞታው
መቼም ላይቀርልኝ ሀሜታው
እቴ በነጠላሽ በጥልፉ በጥልፉ
እቅፍ አርጊኝ እና ይውሰደኝ እንቅልፉ
ያለልሽ አዝማሪው ትዝ አለኝ አንቺዬ
ስታማ ነበር በእሷ ነው ተብዬ
ያለልሽ አዝማሪው ትዝ አለኝ አንቺዬ
ስታማ ነበር በእሷ ነው ተብዬ
አይኗን ቀጠን አርጋ ተኩላው (ተኩላው)
አይኗን ዐየ ጎበዝ አይኑን ቢያመው መንገድ ሳተ (ሳተናው)
አይኗን ቀጠን አርጋ ተኩላው (ተኩላው)
አይኗን ዐየ ጎበዝ አይኑን ቢያመው መንገድ ሳተ (ሳተናው)
የሀገሬው ጎበዝ ወንድ ልጅ
እንደ እሳት ቁጡ የሚፋጅ
ሁሉን ገጣሚ እጅ በእጅ
በአንቺ ተይዞ ጠና ደጅ
ለሰሚ አይሆን ለወሬ አይበጅ
አንቺን ያሙ እለት ቀሩ ከደጅ
ሀገሩማ ያውቃል ምስክር ነው
ቀሚስሽማ የጨዋ ነው
ለሀሜተኛ ሰው መድኃኒቱ
ማቀፍ አይደለም ወይ ብልሀቱ
እቴ በነጠላሽ በጥልፉ በጥልፉ
እቅፍ አርጊኝ እና ይውሰደኝ እንቅልፉ
ያለልሽ አዝማሪው ትዝ አለኝ አንቺዬ
ስታማ ነበር በእሷ ነው ተብዬ
ያለልሽ አዝማሪው ትዝ አለኝ አንቺዬ
ስታማ ነበር በእሷ ነው ተብዬ
እቴ በነጠላሽ በማጉ በድሩ (በማጉ በድሩ)
እቅፍ አርጊኝና ልበል ደህና እደሩ (ልበል ደህና እደሩ)
እቴ ደረትሽ በማሉ በማሉ (በማሉ በማሉ)
ድግፍ አርጊኝና ያሉትን ይበሉ (ያሉትን ይበሉ)
እቴ በነጠላሽ በማጉ በድሩ (በማጉ በድሩ)
እቴ በነጠላሽ በጥልፉ በጥልፉ
እቅፍ አርጊኝ እና ይውሰደኝ እንቅልፉ
ያለልሽ አዝማሪው ትዝ አለኝ አንቺዬ
ስታማ ነበር በእሷ ነው ተብዬ
ያለልሽ አዝማሪው ትዝ አለኝ አንቺዬ
ስታማ ነበር በእሷ ነው ተብዬ
Random Song Lyrics :
- h e a d u p ft. fanaticus - jamil lyrics
- fuck_that smile (bless the adventure) - johjoh lyrics
- b.m.a. - mik brown lyrics
- fogo - mari duarte lyrics
- c.s.i.e. - mick jenkins lyrics
- i got you - jaime woods lyrics
- shawty u know what it do - yung lean lyrics
- inimigos - innatuz lyrics
- carry me - kygo lyrics
- uzi - lil durk lyrics