![lirikcinta.com](https://www.lirikcinta.com/statik/logonew.png)
yeznah - haleluya tekletsadik lyrics
በጣም ምወደው ወይኔ ወይኔ ወይኔ በጣም ነው ምወደው። እሱ ሰውዬ ብታየው አጭር ነው እኔ እንኳን አጭር አልወድም ነበር ምን እንደጣለብኝ አላቅም ያኔ።
የዝናህ የዝናህ የዝናህ የዝናህ
የዝናህ የዝናህ የዝናህ የዝናህ
እኔም እንደ አስናቁ ሆነብኝ እድሌ
ካጭሩ ጋር ሆነ የፍቅር ገድሌ
የማሪያ ሞንቴዝ ባይሆንም ዘመኑ
እኔንም ማርኮኛል በዝና ጅንኑ
የዝናህ የዝናህ የዝናህ የዝናህ
የዝናህ የዝናህ የዝናህ የዝናህ
አጭር ወንድ አልወድም እንዳላልኩኝ ‘ባፌ
ይኸው ጉዴን እዩት ‘ባጭሬ ከንፌ
ፍቅር ጥበብ አለው ደሞ ማዳን ገሎ
አንጀቴን ካራሰው ለምኔ መለሎ
አይይይይይይ
የዝናህ የዝናህ የዝናህ የዝናህ
የዝናህ የዝናህ የዝናህ የዝናህ
ተንጠራርቶ ስሞኝ ባራዳ ልጅ ሙያ
ረጅም ጎምላላውን አሰኘኝ ኧረዲያ
አሁን ገና ገባኝ የአስኔ ፍቅር ውሉ
ኮረሪማ ወዶ ደርሶ መዋለሉ
የዝናህ የዝናህ የዝናህ የዝናህ
የዝናህ የዝናህ የዝናህ የዝናህ
በጃንሆይ ግርማ መኮንንነቱ
ሁለመናው ቢያምር ተረሳኝ ቁመቱ
የማነች ይሉኛል ስሜ ነው ዘንካታ
እጥር ምጥን ያለ ይሆናል መከታ
ጃን ሜዳ አይበቃውም ሲሄድ በጎዳናው
ፍረዱኝ ያያቹ ልብ ነው ቁመናው
ቀማችው ይሉኛል የቀማኝ እሱ ነው
ልቤን አሸፍቶ እታች የነጠቀው
ሲስመኝ ባያቹ ሲመራኝ ባያቹ
አጭር ነው ቁመቱ መቼም ባል ያላቹ
መመተሪያ ሆኗል ለኔማ የወንዱ
በሱ የተለካ ሊታይ ነው ጉዱ
lyrics provided by
Random Song Lyrics :
- nutmeg (freestyle) - ludacris lyrics
- mar de estrelas - fafá de belém lyrics
- hashtag - curt kennedy lyrics
- list do m - edzio lyrics
- vittu mä pelkään sua (tranz4muhz remix) - laveerre lyrics
- beasty ft. tulsa jack - franco bambino lyrics
- take it easy!/roman - michi lyrics
- mermaids - blaq tuxedo lyrics
- nostrand - weekend money lyrics
- closer [live 2018] - lacuna coil lyrics