amnalew - chelina lyrics
ላይሆን ላይሳካ የማልመዉ
ምን ቤት ነኝ እንዲህ የምደክመው
አይደለሁ ደሞም እድለኛ
የምን መቅበጥ ነው እንደነ እንትና
ቤተሰብ አይረዱ ጓደኞች እንዲሁ
ሙድ ይዘው እዛ ይዘው ከበው እየሳቁ
እንዲህ ሚሉ ድምፆች ቢመጡም
ግን አምናለው አሁንም ምክንያቱም
ኣምኖ መሞት ይሻለኛልና
መርጫለው መባል ____
ለኔ ጥበብ ነዉ ለነሱ ሞኝ የሆነው
ለዚህ ነዉ ቢሉ ቢሉ ቢሉ ቢሉ የማልሰማዉ
የኛ አዋቂ ኢ ኢ ኢ ኣይ ጥበበኛ
አ ቢሉ ቢሳለቁ አላፍር አልፈራ
የሚያየኝን ሳየው ሸክሜን ስጥለው
ከባድ ብዬ ያሰብኩት እንዴት ቀሊል ነዉ
ቢያዝልም ማየት ማመን ነዉና
የታለ ለሚሉኝ አሁንም እንደገና
ኣምኖ መሞት ይሻለኛልና
ምርጫዬ ይህ ነው ባይሆን ባይሳካ
ሕልሜን ሁሉም በጊዜው ይረዳል
ልቤ ቆም አይኔ ቦግ ትኩር ብሎ አይቷል
እርስቱም መሻሉን ኧረ አያይ
የሆኑ ያመኑም አሉ በዙሪያዬ
በልጅነቴ በልቤ ዉስጥ ቤቱን የሰራ
የነፍሴን ልጓም ይዞ በድንግዝግዝ የሚመራ
ካጀቡ ለይቶኝ አዲስ መንገድ የሰጠኝ(የሰጠኝ)
ግን ሲፈታ የሚገለጥ ታላቅ ውጥን እኔ ህልም አለኝ
ለሌላዉ ህልሜ ባይገባ ቢሰወር ቢደበቅ ግልፅ ነው ለኔ
ለሚሆነው ለምን ከላይ የሚፈታ ነገ በዘዴ
መክሊቴን እኖራለዉ
ሆኖ አየዋለው
አዎ ሀሳቤ በኔ እውን ይሆናል
ነገ ህልሜ ይታያል ይፈታል
አልቆምም ለምንም
እሮጣለው
ሲሰምር ሲሞላ
አያለው
ዛሬ ሀሳቤን
እኖራለው
ህልሜ ይፈታል
ይህን አቃለው
Random Song Lyrics :
- noche - aladin 135 lyrics
- jolly - daytona kk lyrics
- på väg att dö - lillasyster lyrics
- hello, central - peter tork and shoe suede blues lyrics
- you and i (1996) - the monkees lyrics
- a song about extreme violence and sexual content - slump satan lyrics
- the porpoise song - micky dolenz lyrics
- talent's a myth - ruslan lyrics
- running free - mycha, kylie & denzel jo lyrics
- yokai - mol$ lyrics