![lirikcinta.com](https://www.lirikcinta.com/statik/logonew.png)
salaysh - bezuayehu demissie lyrics
አይቶ ጠግቦ ከዳት ባሉኝ ሰዎች ሳያውቁ ባወሩት ብዙ አዝኛለሁ
እነዴት ብዬ አንችን ፍቅሬን ጥዬ በምን አቅሜ ችዬ መውደዴን እሰዋለሁ
አይቶ ጠግቦ ከዳት ባሉኝ ሰዎች ሳያውቁ ባወሩት ብዙ አዝኛለሁ
እነዴት ብዬ አንችን ፍቅሬን ጥዬ በምን አቅሜ ችዬ መውደዴን እሰዋለሁ
ወሬ የሚሰፍሩልሽ እንደ ማኛው ስንዴ
ከምውድሽ በላይ ይወዱሻል እንዴ
አያፈቅሩሽ ፍቅሬን ከልቤ ቢቀሙኝ
ምንም አያገኙ እኔን ላንቼ ሚያሙኝ
አንለይም እኛ ያም አለ ያም አለ
በ’ለቀቅ አድረገው ቢተውኝ ምን አለ
ሳላይሽ ሳላይሽ ማመኔን ሳላይሽ ሃሳብ ያደክመኛል
ሳላይሽ ብሰማማ ወሬ ሳላይሽ ጨርቅ ያስቀድደኛል
ሳላይሽ ሳላይሽ ማመኔን ሳላይሽ ሃሳብ ያደክመኛል
ሳላይሽ ብሰማማ ወሬ ሳላይሽ ጨርቅ ያስቀድደኛል
አይቶ ጠግቦ ከዳት ባሉኝ ሰዎች ሳያውቁ ባወሩት ብዙ አዝኛለሁ
እነዴት ብዬ አንችን ፍቅሬን ጥዬ በምን አቅሜ ችዬ መውደዴን እሰዋለሁ
አይቶ ጠግቦ ከዳት ባሉኝ ሰዎች ሳያውቁ ባወሩት ብዙ አዝኛለሁ
እነዴት ብዬ አንችን ፍቅሬን ጥዬ በምን አቅሜ ችዬ መውደዴን እሰዋለሁ
አናጠፋም ደፍተን የፍቅርን መረቆን
እናውቅበታለን ከፍቶን መታረቆን
ከሌላ ቢመጣም ስምምነታችን
አላገናኘንም አምላክ እኔና’ችን
ጠብ እርግፍ አንበል ለነገር እንግዳ
ጓዳውን ለፍቅር እስኪ እናሰናዳ
ሳላይሽ ሳላይሽ ማመኔን ሳላይሽ ሃሳብ ያደክመኛል
ሳላይሽ ብሰማማ ወሬ ሳላይሽ ጨርቅ ያስቀድደኛል
ሳላይሽ ሳላይሽ ማመኔን ሳላይሽ ሃሳብ ያደክመኛል
ሳላይሽ ብሰማማ ወሬ ሳላይሽ ጨርቅ ያስቀድደኛል
Random Song Lyrics :
- yeah!* - pe$o pete lyrics
- is it me? - the living tombstone lyrics
- hurt - odd beholder lyrics
- on the last day - inexorum lyrics
- division - cal scruby lyrics
- whap whap (remix) - jdot breezy lyrics
- woven in fragments of putrid disgust - hideous miscreation lyrics
- blue & black - various artists lyrics
- when christmas has come and gone - jake hoot lyrics
- aual na8ra | أول نظرة - cuseng lyrics